👉🏽የተጎዳን የአካል ክፍል (እጅና እግር) በጨርቅ አጥብቀው በሚያስሩበት ጊዜ የደም ዝውውር የበለጠ እንዲገታ በማድረግ ወደ ጋንግሪን (የሰውነት መበስበስ) ይቀየራል፡፡ በመሆኑም የተጎዳውን አካል ለመደገፍ የምንጠቀመው ድጋፍ በሙሉ ከተቻለ ዙሪያውን ዞሮ የሚታሰር መሆን የለበትም፡፡ አካሉን ደግፎ እንዲይዝ ብቻ ላላ መደረግ አለበት፡፡

ደም ለማቆም ጥምጣም (tourniquet) አይጠቀሙ!
ደም ለማቆም ሲባል በተጎዳው አካል ላይ ጥምጣም መጠቀም በደም ዝውውር ላይ ጫና ያሳድራል፡፡ ስለዚህ የሚፈስ ደም ለማቆም ሲያስቡ ጨረቅ በመደራረብ መሸፈንና የተጎዳውን እጅ ወይም
እግር ወደ ላይ ከፍ የሚያደርግ ነገር ብቻ ይጠቀሙ፡፡ ከዚያም ተጎጂውን/ዋን ልጅ ወደ ጤና ተቋማት በአፋጣኝ ይላኩ፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *